Get Mystery Box with random crypto!

በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገፆች የድርጅታችን አውቶብስ ላይ አደጋ መድረሱንና የሰው ህይወት ማለፉ | YeneTube

በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገፆች የድርጅታችን አውቶብስ ላይ አደጋ መድረሱንና የሰው ህይወት ማለፉን የሚገልፅ የተሰራጨው መረጃ ሃሰት ነው-አንበሳ የከተማ አውቶብስ አገልግሎት ድርጅት

ማምሻውን በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገፆች የድርጅታችን አውቶብስ ላይ አደጋ መድረሱንና የሰው ህይወት ማለፉን የሚገልጽ የተሰራጨው መረጃ ሃሰት መሆኑን አንበሳ የከተማ አውቶብስ አገልግሎት ድርጅት አስታውቋል ።

ከ ሁለት አመታት በፊት የተፈጠርውን አደጋ ዛሬ የተፈጠረ በማስመሰል የሃሰት እና የሽብር መረጃ ለማህበረሰቡ የማዛመት ስራ እየተሰራ መሆኑን ድርጅቱ ገልጿል።

ማህበረሰቡ ያልተረጋገጡ መረጃዎችን ከማጋራትም ሆነ በመረጃዎቹ ከመረበሽ መቆጠብ እንዳለበት እና አላስፈላጊ ሽብር ለመፍጠር የሃሰት መረጃ የሚያሰራጩ ሚዲያዎችም ሆነ ግለሰቦች ከድርጊታችሁ እንዲቆጠቡ ድርጅቱ አሳስቧል ።

@YeneTube @FikerAssefa