Get Mystery Box with random crypto!

መሰረታዊ የጤና ትምህርትን ኅብረተሰቡ በነፃ የሚያገኝበት ማዕከል ተመረቀ፡፡ ‹‹የጤና ትምህርት ለ | YeneTube

መሰረታዊ የጤና ትምህርትን ኅብረተሰቡ በነፃ የሚያገኝበት ማዕከል ተመረቀ፡፡

‹‹የጤና ትምህርት ለሁሉም›› በሚል መሪ ቃል በተጀመረው የማኅበረሰብ የጤና ስልጠና ማዕከል ለህብረተሰቡ ውስብስብ ባልሆኑ እና አሳታፊ በሆኑ መንገዶች የጤና እውቀት ማስጨበጫ ይሰጣልም ተብሏል፡፡

iTena(አይ ጤና) በተሰኘው ተቋም የሚሰጠው ይህ አገልግሎት ከዚህ ቀደም የጤና ትምህርት የጤና ባለሙያ መሆን ለሚፈልግ ሰው ብቻ መሰጠቱን የሚያስቀር መሆኑም የተቋሙ መስራችና ዋና ስራ አስኪያጅ ዶ/ር እየሩሳሌም ማሞ ገልፀዋል።

በማዕከሉ ወሳኝ የጤና ትምህርት ናቸው ተብሎ በሚታመንባቸው የጤናማ አመጋገብ ስርዓቶች፣ የስነ ተዋልዶ እና የቤተሰብ ምጣኔ ትምህርቶች፣ እንደ ስኳር እና የደም ግፊት አይነት ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ፣እንደ ሰሞነኛው የኮቪድ 19 ወረርሽኝ አይነት ተላላፊ በሽታዎች እና ሌሎችም ትኩረት ተደርጎ ይሰጣልም ብለዋል።

በተጨማሪም ከበሽታ መከላከያ ትምህርቶች ባሻገር በተለያዩ በሽታዎች ለተጠቁ የህብረተሰብ ክፍሎች በሽታው የባሰ ጉዳት እንዳያደርስባቸው ማድረግ ስላለባቸው ጥንቃቄዎች እና አጠቃላይ ማንቃት ላይ ያተኮሩ ትምህርቶች እንደሚሰጡም አሳውቀዋል።

ይህም በቀላሉ ሊድኑ በሚችሉ በሽታዎች ሕይወታቸው የሚያልፍ ዜጎችን ቁጥር ለመቀነስ ከፍተኛ ሚና እንዳለው ነው የተነገረው፡፡

iTena(አይ ጤና) በ አራት ሃኪሞች የተመሰረተ እና ለማህበረሰቡ የቆመ ድርጅት መሆኑን የሚገልፅ ሲሆን ከዚህ አገልግሎት በተጨማሪም የህክምና ጥሪ ማዕከል፣ የቤት ለቤት ህክምና እነዲሁም እና ተቋማት ላይ ያተኮረ የጤና አገልግሎትን በመስጠት ላይ እገኛለሁ ብሏል፡፡

[አሐዱ]
@YeneTube @FikerAssefa