Get Mystery Box with random crypto!

ደብረ ሲና ሌሎች የአካባቢው ከተሞች የኤሌክትሪክ አገልግሎት አገኙ! የአማራ ክልል ኤሌክትሪክ አገ | YeneTube

ደብረ ሲና ሌሎች የአካባቢው ከተሞች የኤሌክትሪክ አገልግሎት አገኙ!

የአማራ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከወራሪው ቡድን ነፃ የሆኑ ከተሞችንና የገጠር አካባቢዎችን እንደገና የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ ለማድረግ ርብርብ እያደረገ ይገኛል፡በዚሁ መሰረት በዛሬው ዕለት ደብረ ሲና፣ ጣርማ በር፣ የለን፣ ተሬ፣ ራሳ፣ ኩማሜ እና በሸዋ ሮቢት ዙሪያ ያሉ ሌሎች የገጠር ከተሞች የኤሌክትሪክ ኃይል አግኝተዋል፡፡

የትህነግ ቡድን ሰሜን ሸዋ ዞን በገባበት ወቅት የወደሙና የተጎዱ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶችን በመጠገንና መልሶ በመገንባት ኤሌክትሪክ እንዲያገኙ ለማድረግ የደብረ ብርሃን ዲስትሪክት ሰራኞች ከፍተኛ ርብርብ እያደረጉ ነው፡፡በዚህም የመካከለኛ እና የዝቅተኛ መስመር ፍተሻና ጥገና ተጠናቆ የተጠቀሱት አካባቢዎች ኤሌክትሪክ ማግኘታቸውን የዲስትሪክቱ ዳይሬክተር አቶ ሙሉጌታ ደሳለኝ መናገራቸውን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa