Get Mystery Box with random crypto!

YeneTube

የሰርጥ አድራሻ: @yenetube
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 130.37K
የሰርጥ መግለጫ

መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2024-04-18 16:58:08
ኔስትሊ በማደግ ላይ ላሉ ሀገራት በሚልካቸው የወተት ምርቶቹ ላይ ስኳር እንደሚጨምር ተሰማ!

የስዊዘርላንዱ የምግብና መጠጥ አምራች ኩባንያ ኔስትሊ ወደ አፍሪካ፣ እስያ እና ደቡብ አሜሪካ በሚልካቸው የጨቅላ ህጻናት ወተት እና ሌሎች ምርቶቹ ላይ ስኳር እና ማር እንደሚጨምር "ፐብሊክ አይ" የተሰኘ ስዊዘርላንድ ውስጥ የሚገኝ የምርመራ ትቋም አጋልጧል።

ቡድኑ ከላይ ወደተጠቀሱት ክፍለ አህጉራት የሚላኩ የኒዶ(Nido) እና ሴሪላክ(Cerelac) ምርቶችን ቤልጄም ወደሚገኝ ላብራቶሪ ልከው ያስመረመሩ ሲሆን በውስጡ በአለም የጤና ድርጅት መመሪያ መሰረት አለቅጥ መወፈርን እና ተያያዝ በሽታዎችን ለመከላከል ለጨቅላ ህጻናት የተከለከለ የስኳር መጠንን ይዞ መገኘቱ ተዘግቧል። በአንጻሩ ኩባንያው ለአውሮፓ ደምበኞቹ የሚልከው ስኳር የሌለበት እንደሆነ የዘ ጋርዲያን ዘገባ ያመለክታል።

ታይምስ ኦፍ ኢንዲያ የተባለው ጋዜጣ እንደዘገበው ከሆነ ደግሞ በሴሪላክ ምርት ላይ የሚጨመረው ስኳር መጠን ከፍተኛ ከሆነባቸው ሀገራት አንዷ ኢትዮጵያ መሆኗን ያመለክታል።የመረጃው ይፋ መሆንን ተከትሎ የአለም ጤና ድርጅት ባለሙያዎች የተቹት ሲሆን እስካሁን ኩባንያው ያለው ነገር የለም።

@YeneTube @FikerAssefa
13.2K viewsedited  13:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-18 16:01:10
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት በፍልስጤም አባልነት ላይ ነገ ድምፅ ይሰጣል!

የፀጥታው ምክር ቤት የፍልስጤምን የተባበሩት መንግስታት ሙሉ አባልነት ላይ ድምጽ ለመስጠት ለመጭው አርብ ቀጠሮ ይዟል።በአሁኑ ጊዜ ከ10 ተዘዋዋሪ አባላት አንዷ የሆነችው አልጄሪያ «የፍልስጤም ግዛት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አባል እንድትሆን» የሚል ጥያቄ አቅርባለች።የአልጄሪያን ጥያቄ ተከትሎ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት በፍልስጤም አባልነት ላይ በነገው ዕለት ድምፅ እንደሚሰጥ ሮይተርስ የዜና ምንጭ ዘግቧል።

15 አባላት ያሉት የፀጥታው ምክር ቤት ነገ ዓርብ ከጠዋቱ 3 ሰአት ላይ፤«የፍልስጤም ግዛት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት አባል ሆና እንድትገባ”በቀረበው ረቂቅ የውሳኔ ሃሳብ ላይ ድምፅ ይሰጣል ሲል ሮይተርስ ዲፕሎማቶችን ጠቅሶ ዘግቧል።

እንደ ሮይተርስ ዘገባ የምክር ቤቱ ውሳኔ ቢያንስ ዘጠኝ የድጋፍ ድምጽ የሚያስፈልገው ሲሆን ፤እርምጃው እስከ 13 የምክር ቤት አባላት ድጋፍ ሊኖረው ይችላል ተብሎ ይጠበቃል።ይህም ሀሳቡን በመቃወም ዩኤስ አሜሪካ ድምፅን በድምፅ የመሻር መብት እንድትጠቀም ያስገድዳል ሲል ሮይተርስ በዘገባው አመልክቷል።

[DW]
@YeneTube @FikerAssefa
13.1K views13:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-18 12:53:42
ቀሲስ በላይ መኮንን በተጠረጠሩበት በሀሰተኛ ሰነድ ከ6 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገንዘብ ዝውውር ወንጀል ለምርመራ ማጣሪያ ጊዜ ቀጠሮ ተፈቀደ!

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ቀሲስ በላይ መኮንን በተጠረጠሩበት በሀሰተኛ ሰነድ የዶላር ዝውውር ወንጀል ለምርመራ ማጣሪያ ጊዜ ቀጠሮ መፍቀዱ ተሰምቷል፡፡

የፌደራል ፖሊስ መርማሪ ቀሲስ በላይ መኮንን ከትናንት በስቲያ በአፍሪካ ህብረት ቅጥር ጊቢ ውስጥ በሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ውስጥ በአካል ቀርበው ሀሰተኛ የክፍያ ሰነዶችን በመያዝ ለ3 ግለሰቦች እና ለአንድ የግል ድርጅት ሒሳብ 6 ሚሊየን 50 ሺህ ዶላር ሊያዘዋውሩ ሲሉ በአፍሪካ ህብረት ሴኪዩሪቲዎች ተይዘው ለፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ተላልፈው መሰጠታቸውን ጠቅሶ የጥርጣሬ መነሻውን ለችሎቱ ማቅረቡን ዳጉ ጆርናል ከፋና ዘገባ ተመልክቷል።

በዚህ መነሻ መሰረትም መርማሪ ፖሊስ ተጨማሪ የምርመራ ማጣሪያ ሥራ ለማከናወን የ14 ቀን ጊዜ ቀጠሮ እንዲሰጠው ጠይቋል።ተጠርጣሪ ቀሲስ በላይ መኮንን ድርጊቱ መፈጸሙን አምነው፤ ይሁን እንጂ ወንጀል አለመፈጸማቸውን አስረድተዋል።ስለሆነም የዋስትና መብታቸው እንዲፈቀድላቸው ጠይቀዋል።የግራ ቀኝ ክርክሩን የተመለከተው ጊዜ ቀጠሮ ችሎቱ ተጠርጣሪው ያቀረቡትን የዋስትና ጥያቄ በማለፍ ለፖሊስ የ7 ቀናት የምርመራ ፈቅዷል።

@YeneTube @FikerAssefa
13.4K views09:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-18 12:14:47
የዉጪ ባለሃብቶች ከማዳበሪያ እና ከነዳጅ በስተቀር በሁሉም የንግድ ኢንቨስትመንት ዘርፎች ላይ እንዲሳተፉ ተፈቀደ!

መሰረታቸውን በዉጪ ያደረጉ ባለሃብቶች በችርቻሮ እና በጅምላ ንግድ ላይ እንዲሳተፉ ፍቃድ መሰጠቱን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሸን እና የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር በጋራ አስታውቀዋል።

ከጅምላ ንግድ ጋር ተያይዞ ከማዳበሪያና ከነዳጅ ጅምላ ንግድ በስተቀር በሁሉም አይነት የጅምላ ንግድ መስኮች መሰማራት ይችላሉ ተብሏል በዚህም በጥሬ ቡና፣ በቅባት እህሎች፣ ጫት፣ ጥራጥሬ፣ ቆዳ እና ሌጦ፣ የደን ውጤቶች እና የቁም እንስሳት የመላከ የወጪ ንግድ ላይ እንዲሳተፉ ነዉ የተፈቀደው ።

ከዚህ ቀደም ለአገር ውስጥ ባለሃብቶች ብቻ ተከልለው የቆዩ የወጪ፣ የገቢ፣ የጅምላ እና የችርቻሮ ንግድ ዘርፎች አሁን ደግሞ ለውጭ ባለሃብቶች ከፍት እንዲሆኑ መደረጉ ነዉ ለማወቅ የተቻለው።

Via Capital
@YeneTube @FikerAssefa
13.1K views09:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-18 10:33:32 የኮሌራ ወረርሺኝ በኢትዮጵያ በ8 ክልሎች የሚገኙ ከ41 ሺህ በላይ ዜጎችን ማጥቃቱን የዓለም ጤና ድርጅት ገለጸ፡፡

ከፍተኛ ረሃብ እና በሽታ የብዙ ኢትጵያዊያንን ህይወት አደጋ ላይ መጣሉን የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ተናግረዋል፡፡የትግራይ፣ አማራ፣ አፋር፣ኦሮሚያ እና ሌሎች ክልሎች በኢትዮጵያ በተከሰተዉ ጦርነት ምክንያት ከባድ ቀዉስን ያስተናገዱ ናቸዉ፡፡

በእነዚህ ክልሎችም የጤና አገልግሎት መስጫ ማዕከላት እና መሰረተ ልማቶች ሙሉ ለሙሉ አልያም በከፊል መዉደማቸዉንም ነዉ ድርጅቱ የገለጸዉ፡፡በኢትዮጵያ 20ኛወሩን ያስቆጠረዉ የኮሌራ ወረርሺኝ 41ሺህ ዜጎችን ያጠቃ እና በ8ወረዳዎች የተከሰተ መሆኑንም ድርጅቱ አስታዉቋል፡፡

የአሁኑ የኮሌራ ወረርሺኝ በኢትዮጵያ ታሪክ ከፍተኛዉ መሆኑን ነዉ ዶ/ር ቴዎድሮስ የተናገሩት፡፡በሌላ በኩል ደግሞ በወባ ወረርሺኝ 1.1 ሚሊየን ዜጎች መያዛቸዉን አንስተዉ ፤ ባለፈዉ ዓመት ከተመዘገበዉ 4 ሚሊየን ቁጥር አሁን ላይ መቀነሱን ነዉ ያስታወቁት፡፡

በዚህኛዉ ዓመት ብቻ ከ1መቶ በላይ በሚሆኑ አከባቢዎች ከ15ሺህ በላይ ሰዎች በኩፍኝ ወረርሺኝ መያዛቸዉንም አንስተዋል፡፡እነዚህ ችግሮች እየተከሰቱ ያሉት ሚሊየኖች መሰረታዊ የሆነ የህክምና አገልግሎት በሚፈልጉባቸዉ ቦታዎች መሆኑንም ነዉ የገለጹት፡፡

[Ethio FM]
@YeneTube @FikerAssefa
13.2K views07:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-17 21:10:36
በአዲስ አበባ ከተማ ተቋርጦ የነበረው የመታወቂያ መስጠት እና እድሳት አገልግሎት በቀጣዩ ሳምንት ዳግም ይጀመራል ተባለ!

በአዲስ አበባ ከተማ ከአንድ ሳምንት በላይ ተቋርጦ የቆየውን የመታወቂያ መስጠት እና እድሳት አገልግሎትን በሚቀጥለው ሳምንት ለመጀመር የጥገና ስራ እያከናወነ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ገለጸ። ኤጀንሲ ይሰጣቸው የነበሩ መደበኛ አገልግሎቶች የተቋረጡት፤ ከመረጃ ማከማቻ ቋቱ ጋር በተገናኙ “የቴሌኮም ኬብሎች” ላይ ጉዳት በመድረሱ መሆኑን ገልጿል።

በአዲስ ከተማ አስተዳደር የሚገኘው የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ፤ የመታወቂያ ስርጭት፣ የልደት እና የሞት ምዝገባ፣ ያላገባ የምስክር ወረቀት፣ የማስረጃ የማረጋገጥ ስራን እንዲሁም የጋብቻ እና የፍቺ ምዝገባን የሚከውን ተቋም ነው። ኤጀንሲው በመዲናዋ የሚገኙ 106 ወረዳዎችን “በዲጂታል” ስርዓት” በማስተሳሰር ይሰጣቸው የነበሩ አገልግሎቶች፤ ካለፈው አንድ ሳምንት ወዲህ በመቋረጣቸው በተገልጋዮች ላይ መጉላላትን አስከትሏል።

በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ ሶስት የሚገኝ የነዋሪነት ምዝገባ ጽህፈት ቤትን በትላንትናው ዕለት በአካል ተገኝቶ የተመለከተው የ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ዘጋቢ፤ ለወትሮ በሰው ብዛት ይጨናነቅ የነበረው አገልግሎት መስጪያ ባዶ መሆኑን ታዝቧል። አገልግሎት መቋረጡን ባለመስማት ወደ ጽህፈት ቤቱ የመጡ ሁለት ነዋሪዎችም እምብዛም ሳይቆዩ መመለሳቸውንም ተመልክቷል።

[Ethiopia Insider]
@YeneTube @FikerAssefa
15.0K views18:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-16 20:55:37
ማስጠንቀቂያ! ቪዲዮውን ከ 18 ዓመት በታች የሆኑ ሰዎች እንዲያዩት አንመክርም።

በሲድኒ፣ አውስትራሊያ የሚገኝ አንድ ቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ላይ እያለ አንድ ቢላዋ የያዘ ሰው በአንድ ቄስ ላይ በትናንትናው ዕለት ጥቃት ሰነዘረ።

ይሄ ሰው በዋኪሊ በሚገኘው የደጉ እረኛ ቤተክርስቲያን ቀርቦ ጳጳስ ማሪ ኢማኑኤልን ደጋግሞ በስለት ወግቷቸዋል።

ጥቃት አድራሹ ቄሱን ለመዳን የሞከሩ አራት ምእመናን ላይም ጥቃት ፈፅሟል። ቄስ ማሪ ኢማኑኤል ጉዳት ቢያጋጥማቸውም ከመሞት ተርፈዋል ሲሉ የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

ይሄ ሰው ከአንድ ቀን አስቀድሞ አንድ ሰው በሲድኒ የገበያ ማእከል ውስጥ ገሎ መሰወሩም ተነግሯል።
12.9K views17:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-16 19:16:43
ጥገኝነት ጠያቂዎችን ወደ ሩዋንዳ ለማዛወር እንግሊዝ የነደፈችው ረቂቅ ሕግ ሊጸድቅ ነው!

ብሪታንያ ጥገኝነት ጠያቂዎችን ወደ ሩዋንዳ ለማዛወር የያዘችው እና ከፍ ያለ ተጽዕኖ እንደሚያሳድር የታመነው ዕቅድ የሃገሪቱ ሕግ ሊሆን ተቃርቧል። የዕቅዱ ተቃዋሚዎች በአንጻሩ ስደተኞቹን በኃይል ከአገር የማስወጣቱን ውጥን ማገድ የሚችል አዲስ የሕግ መቋቋሚያ ለማበጀት ጥረት ይዘዋል።

የጠቅላይ ፍርድ ቤቱን እገዳ ተጽዕኖ ለማስቀረት እና በላይኛው ምክር የቀረበውን ተቃውሞ ለመቋቋም የታለመው ይህ ሕግ በያዝነው ሳምንት በሃገሪቱ ፓርላማ ይድቃል ተብሎ ተጠብቋል።

‘የሩዋንዳ ዕቅድ’ የሚል ቅጽል የተሰጠው ይህ ውጥን ጠቅላይ ሚንስትር ሪሺ ሱናክ ‘ሕገ ወጥ ስደተኞችን ወደዚያች አገር የሚያጓጉዙ ጀልባዎች እንቅስቃሴ’ ለማስቆም ለገቡት ቃል ‘ወሳኝ እርምጃ ነው’ ተብሏል።

ጉዳዩን አመልክቶ አስተያየት የሰጡት የሱናክ ቃል አቀባይ ዴቭ ፓሬስ ትናንት ሲናገሩ "የእንግሊዝ ፓርላማ በያዝነው ሳምንት በሕገ ወጥ አስተላላፊዎች ከፍተኛ እንግልት እና ብዝበዛ የሚፈጽምባቸውን ሰዎች ህይወት የሚታደግ ህግ የማጽደቅ እድል ያገኛል" ብለዋል ። “አሁን ባለው አካሄድ መቀጠል እንደማንችል ግልፅ ነው። በመሆኑም ይህ ሁኔታ የሚለወጥበት ጊዜው አሁን ነው” ሲሉም አክለዋል።

በአነስተኛ ጀልባዎች ተጓጉዘው የእንግሊዝ ቻናልን በማቋረጥ ከዚያ የሚደርሱትን ጥገኝ ነት ጠያቂዎች ወደ ምሥራቅ አፍሪካዊቱ አገር ለማዛወር እና በቋሚነትም ኑሯቸውን ከዚያ እንዲያደርጉ በማቀድ ሁለቱ አገሮች የተፈራረሙት ስምምነት ሁለት ዓመታት አስቆጥሯል። በፍርድ ቤት የታገደው ዕቅድ እንግሊዝን በትንሹ 470 ሚሊዮን ዶላር ሊያስወጣት እንደሚችልም ተገምቷል።

Via VoA
@YeneTube @FikerAssefa
13.6K views16:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-16 17:07:26
በቀጣዩ የፈረንጆቹ 2025 ዓመት፤ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ 6.5 በመቶ ያድጋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) ይፋ አደረገ።

IMF ዛሬ ማክሰኞ ሚያዝያ 8፤ 2016 ይፋ ያደረገው ትንበያ፤ ከዘንድሮው አኳያ ሲነጻጸር የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በሚቀጥለው ዓመት አነስተኛ መነቃቃት እንደሚታይበት የሚጠቁም ነው።

በተያዘው የፈረንጆቹ ዓመት፤ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በ6.2 በመቶ ያድጋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ድርጅቱ ባለፈው ዓመት ባወጣው ተመሳሳይ ትንበያ ይፋ አድርጎ ነበር። የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ትንበያ የኢትዮጵያ መንግስት ከሚጠብቀው ዝቅ ያለ ነው። በኢትዮጵያ መንግስት ትንበያ መሰረት፤ በ2016 ዓ.ም. የሀገሪቱ ኢኮኖሚ በ7.9 በመቶ ያድጋል ተብሎ ይጠበቃል። 

(ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
@YeneTube @FikerAssefa
13.5K views14:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-16 15:11:46 በአዲስ አበባ ከተማ በተወሰኑ አካባቢዎች እየተከናወኑ በሚገኙ የኮሪደር ልማት ሥራዎች ምክንያት ዝግ ሆነው የቆዩ መንገዶች ለተሽከርካሪ ክፍት መደረጋቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ።

በዚህም መሰረት፡-

•  ከደጃች ውቤ በአፍንጮ በር ወደ ራስ መኮንን ድልድይ

•  ከባሻወልዴ ችሎት በቱሪስት ሆቴል ራስ መኮንን ድልድይ አፍንጮ በር

•  ከዳኑ ሆስፒታል እስከ ቱሪስት ሆቴል በመውጣት ወደ ራስ መኮንን ድልድይ አፍንጮ በር

•  ከአራዳ መስተዳደር ወደ ዳኑ ሆስፒታል መውረጃ በአንድ አቅጣጫ ብቻ አሽከርካሪዎች መጠቀም እንደሚችሉ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ እየተከናወኑ ባሉ የልማት ሥራዎች ምክንያት ለአጭር ሆነ ለረጅም ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ በጥብቅ መከልከሉን ፖሊስ አስታውቋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
13.7K views12:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ