Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮጵያዬ እንኳን ለድል በዓልሽ አደረሰሽ እኔ ግን ይህን በዓል ለማክበር አልታደልኩም በአንቺ ፊት | ይፈትናል እንጂ ፍቅር ያሸንፋል🇪🇹

ኢትዮጵያዬ እንኳን ለድል በዓልሽ አደረሰሽ እኔ ግን ይህን በዓል ለማክበር አልታደልኩም በአንቺ ፊት ቀና ብዬ በኩራት ለመቆም ገና ብቁ አደለሁም እንኳን ለራሴ ለሌላውም የምተርፍ ልጅሽ አንድ መሆን አቅቶኝ ስቃይ ውስጥ ነው ያለሁት እናቴ እንደ ያኔው እንደ አባቶቼ በፍቅር እና በአንድነት በመተባበር በንፁህ ልብ መቆም አቅቶኝ አቅሜ እየከዳኝ ክንዴ እየተንቀጠቀጠብኝ እግሬ ዝሎብኝ መራመድ አቅቶኝ ብታይኝ እኔ ልጅሽ ሳሳዝን ወንድሜን መውደድ አቅቶኝ ስቃይ ላይ ነኝ ታምሜአለሁ ፊትሽ ቆሜ የድል በአልሽን ለማክበር ሞራል አጣሁ አቃተኝ ግን ልቤን ከጥላቻ ያፀዳው ቀን ጥላቻን ረግጬ ሳሸንፍ ያኔ ነው የኔን አድዋ ድል የማከብረው ያ ካልሆነ አንቺ ፊት የመቆም ሞራሉ የለኝም ጠብቂኝ የኔን አድዋ ድል ለማክበር ጥላቻን ለማሸነፍ የፍቅር ጉዞ ላይ ነኝ ይሄን ድል ለማጣጣም ብዙ የቤት ስራ አለብኝ በአንድነት መቆም ይቀረኛል ትንሽ ታገሺኝ እደርሳለሁ ልቤን ከጥላቻ እና ከመከፋፈል አፅድቼ አንድ የሆንኩ ቀን እመጣለሁ የድል በዓሌን ከአንቺ ጋር ለማክበር ጥላቻን ድል ላድርግ መጀመሪያ። ለማንኛውም ግን እንኳን ለድል በዓልሽ አደረሰሽ መልካም በዓል ይሁንልሽ
ዘለዓለም ያኑርሽ