Get Mystery Box with random crypto!

አንገዛላቹም ብለን አሳፍረን የመለስናቸው እነዛ ነጮቹ ሰዎች ብልህ እንድንሆን አይፈልጉም ምክንያቱም | ይፈትናል እንጂ ፍቅር ያሸንፋል🇪🇹

አንገዛላቹም ብለን አሳፍረን የመለስናቸው እነዛ ነጮቹ ሰዎች ብልህ እንድንሆን አይፈልጉም ምክንያቱም ብልህ ከሆንን ሊበዘብዙን አይችሉማ። በፍቅርና በሰላም እንደ አንድ ማህበረሰብ ተረጋግተን እንድንኖርም አይሹም ምክኒያቱም ስንፋቀርና እርስ በራስችን መዋደድ ስንጀምር ለነርሱ ስጋት እንሆናለን። በወገኖቻችን ጥቃት ለምን ብለን መጠየቅ እንጀምራለን። ይሄ ደግሞ ለነርሱ ትልቅ ህመም ነው። ለዚህም እርስ በርስ በስጋት ዐይን የምንተያይበትን ታሪክና መርዝ በመርጨት የኛን ህይወት በጥብጠው እነርሱ በተድላ ይኖራሉ። "ለምን?" ብለን በብልኃት እንዳንጠይቅ በደካማ ጎናችን ይመጣሉ። በጎሳና በጎጥ አልሳካ ሲላቸው በኃይማኖታዊ ጉዳዮች እየመጡ እረፍት ይነሱናል። እኛም ብልኃቱ ሳይጠፋን በደካማ ጎናችን ስለመጡብን በነሱ የክፋት መረብ ውስጥ ወድቀን እንሰቃያለን...

እኛ እኮ እናሳዝናለን! ግን አያዝኑልንም!